Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:
ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የኮሪደር ልማት አዲስ አበባ፣ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም፡-የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ከአትላስ- ቦሌ መድኃኒዓለም - ብራስ የሚዘልቀውኮሪደር በአጭር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለአገልግሎት ለማብቃት በቀንና በለሊት ክፍለ ጊዜ በትጋት እየሰራ ይገኛል። የኮሪደሩ አጠቃላይ ርዝመት 2 ነጥብ 34 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን በአማካኝ ከ42 እስከ 50 ሜትር የጎን ስፋት አንዲኖረው ሆኖ በራስ ሀይልና በስራ ማህበራት እየተገነባ ይገኛል፡፡ በእስከ አሁኑ የግንባታ ሂደት ከቦሌ መደኃኒዓለም- ብራስ በሁለቱም አቅጣጫ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን የዝናብ ውሃ መፋሰሻ መስመር ትቦ ቀበራ፣ የማንሆል ክዳን ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከቦሌ መድኃኒዓለም - አትላስ በግራና በቀኝ በኩል 960 ሜትር የትቦ ቀበራ በራስ ኃይል ደቡብ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ፅ/ቤት መከናወን ተችሏል፡፡ በቀሪው የመንገዱ ክፍል የመንገድ አካፋይ ከርቭስቶን ስራ፣ የገረጋኒቲ ሙሌት፣ የሰቤዝ ስራና ሌሎች ተያያዥ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በስራ ማህበራት እየተከናወኑ ከሚገኙ ስራዎች መካከል የአፈር ቆረጣ፣የውሃ፣የቴሌና የመብራት መስመሮች ዝርጋትና የእግረኛ መንገድ ዝግጅት ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ኮሪደሩ የሳይክል መንገድ ጨምሮ ምቹ የእግረኛ መንገድ፣ የህፃናት መጫዎቻ ሥፍራ፣የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያና ተርሚናል፣አረንጓዴ ስፍራዎች እንዲሁም ሌሎች የልማት ስራዎችን አካቶ እየተገነባ ይገኛል፡፡
Source :Addis Ababa City Roads Authority
Source Nov 19, 2025