Drive Smarter in Ethiopia: Fact Ethiopia's Traffic Insights

Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:

የመንገድ ጥገና ሥራ እንደቀጠለ ነው

ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፡- የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያየ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አስፋልት መንገዶች እየጠገነ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት የአስፋልት ጥገና ሥራ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል፤ ከዓለም ባንክ ስልጤ ሰፈር፣ ከኮካ አደባባይ አብነት አደባባይ፣ ከአያት አደባባይ - ሰሚት 72፣ ከሰሚት አደባባይ - አያት አደባባይ እንዲሁም ላፍቶ በላይ - ላፍቶ ጊዮርጊስ - ላፍቶ ቪው፣ ከቃሊቲ አደባባይ - አደይ አበባ - ጎተራ ማሳለጫ ይገኙበታል፡፡

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በቀጣይም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙና ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መንገዶች በመለየት የጥገና ስራዎችን በስፋት የሚያከናውን ይሆናል፡፡

Source :AACRA

Source Nov 12, 2025