Drive Smarter in Ethiopia: Fact Ethiopia's Traffic Insights

Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:

የትራፊክ መብራት ቆጠራ እየተከናወነ ነው

የትራፊክ መብራት መጋጠሚያዎች ላይ የትራፊክ ቆጠራ እየተከናወነ ይገኛል


(ት/ማ/ባ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም):- በአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከሚተገብራቸው የአባይት ስራዎች መካከል በከተማዋ በተለያዩ መጋጠሚዎች እ አደባባች ላይ የትራፊክ መብራቶችን በመትከል ተገቢ የሆነ የመንገድ አጠቃቀም ስርዓት በመዘርጋት የመንገድ ትራፊክ ፍሰትን ለማሻሻል እየሰራ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ስራውን በበላይነት እያከናወነ የሚገኘው በባለስልጣን መ/ቤቱ የመንገድ ደህንነት ምህንድስና ዳይሬክቶሬት ሲሆን በመዲናዋ የትራፊክ መብራት መጋጠሚያዎች ላይ የትራፊክ ቆጠራ(Traffic count) ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለትም የ3(ሶስት) ቁጥር ማዞሪያ መጋጠሚያን የትራፊክ ቆጠራ ከውኗል::

መሰል የትራፊክ መብራት ተከላዎችን በከተማዋ ሌሎች አከባቢዎች በማከናወንና ቆጠራ በማካሄድ የፍሰቱን ሁኔታ እያጠናን የተሻለ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲሰፍን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ በመንገድ ደህንነት ምህንድስና ዳይሬክቶሬት የሲቪል መሃንዲስ የሆኑት አቶ ፍሬቃል ንጉሴ አስታውቋል፡፡

Source :TMA

Source Nov 03, 2025