Drive Smarter in Ethiopia: Fact Ethiopia's Traffic Insights

Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:

አውቶማቲክ ትራንስሚሽን

አውቶማቲክ ትራንስሚሽን ያላቸው መኪኖች መንዳት ቀላል እና ምቹ ያደርጉታል። ሆኖም፣ ይህንን ምቾት በረጅም ጊዜ ለመጠቀም፣ መኪናዎን በተሳሳተ መንገድ ከማሽከርከር መቆጠብ አለብዎት። ዛሬ፣ በአውቶማቲክ ትራንስሚሽን መኪና ሲነዱ መራቅ ያለብንን ስህተቶች እና የዚህን ቴክኖሎጂ ዋና ዋና ጥቅሞችን እንመለከታለን።

በአውቶማቲክ ትራንስሚሽን መኪና ሲነዱ ማድረግ የሌለብን ነገሮችየሚከተሉት ልማዶች በአውቶማቲክ ትራንስሚሽን ላይ ከባድ እና ውድ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ፦

• መኪናው ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት ማርሽ መቀየር: መኪናዎ ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት ከድራይቭ (D) ወደ ሪቨርስ (R) ወይም በተቃራኒ አቅጣጫ መቀያየር በትራንስሚሽናችን ላይ ከፍተኛ ጭንቀትና ጉዳት ያደርሳል። ሁልጊዜ መኪናው እስኪቆም ድረስ ይጠብቁ። • መኪናው ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት ወደ ፓርኪንግ (P) መቀየር: ልክ እንደ ላይኛው ነጥብ፣ መኪናችሁ ሙሉ በሙሉ ከመቆሙ በፊት ወደ ፓርኪንግ (P) መቀየር በትራንስሚሽናችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል። የፓርኪንግ ማርሽ መኪናውን በሜካኒካዊ መንገድ ነው የሚያቆመው፣ እና በንቅስቃሴ ላይ ሲጠቀሙበት ስርአቱን ሊሰብር ይችላል። • በኒውትራል (N) ማርሽ ቁልቁለት መውረድ (Coasting in Neutral): ብዙ ሰዎች የነዳጅ ፍጆታን ለመቀነስ በዜሮ ማርሽ ወይም ኒውትራል ቁልቁለት መውረድ እንደሚጠቅም ያምናሉ። ነገር ግን፣ ይህ ልማድ በጣም ከፍተኛ አደጋን ያመጣል! • አደጋው ምንድነው? በአውቶማቲክ ትራንስሚሽን ጊዜ በኒውትራል ማርሽ ቁልቁለትን በምንወርድበት ጊዜ ወደ ትራንስሚሽን የሚገባው የዘይት ስርጭት ይቋረጣል። ይህ ማለት በትራንስሚሽን ውስጥ በቂ ማለስለሻ (lubrication) አይኖርም ማለት ነው። ስለዚህ ትራንስሚሽናችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማሰብ ቀላል ነው። በተጨማሪም፣ መኪናው ላይ ያለዎት ቁጥጥር ስለሚቀንስ ለከፍተኛ አደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ። • መኪናውን ሳይሞቅ ወዲያውኑ መንዳት: ይህ ተግባር በተለይ በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ትራንስሚሽኑ ላይ ጫና ይፈጥራል። ሞተር በሚቀዘቅዝበት ጊዜ በውስጡ ያለው ዘይት በቅዝቃዜ ስለሚወፍር በቀላሉ ተንቀሳቅሶ ክፍሎቹን ማለስለስ አይችልም። ከመንዳትዎ በፊት ለጥቂት ደቂቃዎች ሞተሩ እንዲሞቅ መፍቀድ ትራንስሚሽኑን ጨምሮ ለሁሉም ክፍሎች ጤናማ ነው። • ለረጅም ጊዜ በድራይቭ (D) ላይ አድርጎ መቆም: ለምሳሌ በትራፊክ መጨናነቅ ውስጥ፣ መኪናውን ለረጅም ጊዜ በድራይቭ ማርሽ ላይ እግርዎን ፍሬን ላይ አድርገው መቆየት በትራንስሚሽን ውስጥ ከፍተኛ የሆነ መተፋፈግ (friction) እና ሙቀት (heat) ይፈጥራል። ይህ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያመጣል። ረጅም ጊዜ የሚቆም ከሆነ ወደ ኒውትራል (N) ወይም ፓርኪንግ (P) መቀየር ይመከራል። • ውሃ ወደ ትራንስሚሽን ውስጥ ማስገባት: በፍፁም ውሃ በትራንስሚሽን ውስጥ መግባት የለበትም። ውሃ በትራንስሚሽን ውስጥ የሚገኘውን ዘይት የማለስለስ አቅም በእጅጉ ይቀንሳል፣ ይህም ለከባድ ብልሽት ይዳርጋል።

Source :Admin

Source Oct 23, 2025