Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:
ኢንጅን ወይም የመኪና ሞተር በዉስጡ ባለዉ ሲሊንደር ነዳጅ በማቀጣጠል የሚፈጠረዉን የሙቀት ሀይል ወደ መካኒካል ሀይል በመቀየር የተለያዩ የመኪና ክፍሎች እንዲሽከረከሩ ወይም እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ተሽከርካሪ እንዲንቀሳቀስ የሚያስችል መሰረታዊ የመኪና ክፍል ነዉ።
ኢንጅን(ሞተር) ከሶስት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን እነርሱሞ:- ሲሊንደር ሄድ(ቴስታታ) : ሲሊንደር ብሎክ(ማኖ ብሎክ) እና ክራንክ ኬዝ ናቸዉ።
ሲሊንደር ሄድ(ቴስታታ):- ቫልቮች: ቫልቭ ጋይዶች: ቫልቭ ስፕሪንጎች : ካርቡሬተር ካም ሻፍትና የጭስ ማዉጫ የመሳሰሉት የሚታሰርበት ወይገኝበት የላይኛዉ የሞተር ክፍል ነዉ።
ሲሊንደር ብሎክ(ማኖ ብሎክ):- ሲሊንደር : ፒስተር: ክራንክ ሻፍት: ኮሎ: የዘይት ፊልትሮና ፓምፕ እና ሌሎች የሞተር ክፍሎች የሚገኙበትና ነዳጅ የማቀጣጠል ሂደት የሚካሄድበት የመሀለኛዉ የሞተር ክፍል ነዉ።
ክራንክ ኬዝ:- ሶቶኮፓ ወይም የዘይት ቋት የሚገኝበት ታችኛዉ የሞተር ክፍል ነዉ።
Source :specific
Source Oct 23, 2025