Take control of your journey on Ethiopian roads with Fact Ethiopia. We bring you essential, reliable, and easy-to-understand information on all aspects of Ethiopian traffic. Dive into our extensive resources covering:
" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " - የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
" የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት ወደ ግንባታ ለመመለስ የሚያስችሉ ጉዳዮች እየታዩ ነው " ሲል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳወቀ።
መንገዱ በተለያዩ ምክንያቶች ለጊዜው ተቋርጦ እንደሚገኝ ገልጿል።
አስተዳደሩ ፤ 141 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ፕሮጀክት በዓለም-አቀፉ የሥራ ተቋራጭ ሃይንዳይ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ 4 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዞለት ግንባታው ሲከናወን ቆይቷል ብሏል።
ኾኖም የግንባታው አጠቃላይ አፈጻጸም 62 በመቶ ከደረሰ በኋላ ከወሰን ማስከበር ጋር የተያያዙ ችግሮች በወቅቱ አለመቀረፋቸውን እንዲሁም የግንባታ ውል ዝርዝር ጉዳዮች ላይ የነበሩ አለመግባባቶችን በምክንያትነት በማንሳት የሥራ ተቋራጩ ግንባታውን ለጊዜው እንዳቋረጠ አስረድቷል።
" የመንገድ ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የሚደግፈው የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ከፍተኛ አመራሮች በቀጣይ ቀናት አዲስ አበባ ይገባሉ " ያለ ሲሆን " ግንባታው ዳግም በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር የሚመክሩ ይሆናል " ብሏል።
" ከዚሁ ጎን ለጎን የትራንስፖርት እንቅስቃሴው እንዳይስተጓጎል አስፈላጊ የጥገና ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል። የመንገድ ግንባታው ዳግም እስኪጀመር ድረስም የጥገና ሥራው የሚቀጥል ይሆናል " ሲል አሳውቋል።
ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ኦሮሚያንና ጋምቤላን በኢሉ አባቦር በኩል እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያን በሸካ ዞን በኩል በቅርበት በማስተሳሰር ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያበረክት ነው፡፡
ከዚህ ባሻገር ስድስት ወረዳዎች እና ከ15 በላይ ቀበሌዎችን በቅርበት በማገናኘት ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ትስስር የሚያጠናክር ነው፡፡
Source :tikvahethiopia
Source Oct 23, 2025